በ ዝክረ ቅዱሳት አንስት ዘተዋሕዶ - ፩ የትርጉም ሥራ ላይ የተደረገ የመጽሐፍ ዳሰሳ

ገብረአብ ሓጎስ

Abstract

የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከገዳማትና ገዳማዊ ሕይወት ጋር የተያያዘ ነው። ገዳማት ከሚሰጡት መንፈሳዊና ማኅበረ- ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ጎን ለጎን የቤተ ክርስቲያንንና የሀገርን ታሪክ በመሰነድ ረገድ የራሳቸውን በጎ አስተዋጽኦ አድርገዋል፤ እያደረጉም ነው። ነገር ግን ይህ መረጃን ሰንዶ ለትውልድ የማስቀመጥና የማስተላለፍ ሂደት በሚፈለገው ስፋትና ጥራት ተከናውኖአል ለማለት አይቻልም፡፡ አብዛኛው ትኩረት የአበው ቅዱሳንን ሕይወት ወደመመዝገቡ ያደላ ነው። መጻሕፍቱን በአምስት ክፍል ያዘጋጀው የአቡ ሰይፊን2 የሴቶች አንድነት ገዳምም3 ሆነ የውርስ ትርጉም ባለቤቷ አዜብ በርሄ እንደሚሉት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳት አንስት ተጋድሎ የቅዱሳን አበውን ያክል በስፋት ተነግሯል፤ ተጽፏል ወይም ታውቋል ለማለት እንደማይቻል ይጠቁማሉ። የቅዱሳት አንስትን ድንግልናዊ ሕይወት፣ እንዲሁም ገዳማዊና ምንኵስናዊ ተመክሮ ለቀጣዩ የቤተ ክርስቲያናችን ትውልድ ማስተዋወቁ ፋይዳው ከፍ ያለ ነው፡፡ ለዚህም ነው ይህንን ጽሑፍ ለማዘጋጀት የተነሣሣሁት፡፡

Downloads

Published

2024-05-06

How to Cite

በ ዝክረ ቅዱሳት አንስት ዘተዋሕዶ - ፩ የትርጉም ሥራ ላይ የተደረገ የመጽሐፍ ዳሰሳ: ገብረአብ ሓጎስ. (2024). Journal-of-Ethiopian-Church-Studies/የኢትዮጵያ-ቤተ-ክርስቲያን-ጥናት-መጽሔት-Live/, 9(9), 152–161. Retrieved from https://journals.eotcmk.org/index.php/files/article/view/61