Internal Conflicts within the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church and its Resolutions: The case of two Churches in Addis Ababa Diocese

Kesis Dr. Bitew Kassaw Belay

Abstract

የተለያዩ ሐሳቦች፣ ስጋቶች፣ አመለካከቶችና ግቦች በመኖራቸው ምክንያት ግጭቶች ተፈጥሯዊና የማይቀሩ ናቸው። ሰዎች ተግባራቸውን ለመወጣት አብረው እስከሆኑ ድረስ ግጭቶች ቢፈጠሩ አያስደንቅም። የዚህ ጽሐፍ ዋና ዓላማ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥና መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶችንና ለነዚህ ግጭቶች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጡ የመፍትሔና የውሳኔ ሐሳቦችን አጉልቶ ማሳየት ነው፡፡ በጥናቱ ውስጥ ያሉትን ዓላማዎች ለማሳካት የተለያዩ መረጃዎችን ከተለያዩ ምንጮች በማሰባሰብ ለጥናቱ ግብአት እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ የዚህ ጥናት ቁልፍ የመረጃ ጥልቅ ቃለ ምልልስ ነው። በጥናቱ መረጃ ዘዴ መሠረት ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እስከ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ያሉ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ አገልጋይና ካህናትና ምእመናን ተገቢውን መረጃ በመስጠት ተሳትፈዋል፡፡ ጸሐፊው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በድኅረ 1983 ግጭት የተካሄደባቸውን ለምሳሌ እንደ ገነተ ኢየሱስ እና አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ አብያተ ክርስቲያናትን እንደማሳያ ተጠቅሟል። በተጨማሪም ከእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ጋር አብረው የሚሄዱ ሌሎችንም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በጽሑፉ ተመላክተዋል። የገነተ ኢየሱስና የአንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል አብያተ ክርስቲያናት ሲተዳደሩ የነበሩት በአንድ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ቢሆንም በ1993 ዓ.ም. ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት በግጭት ምክንያት ተለያይተዋል። በሌላ በኩል የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና የመድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሁለት ቢሆኑም ከ1978 ዓ.ም. ጀምሮ በአንድ የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ሥር ተጠቃለው ይገኛሉ። በከላይ የጠቅስናቸውና ሌሎቹም ግጭት የተከሰተባቸው አብያተ ክርስቲያናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የውስጥ ግጭቶች ለማሳየት እንደአብነት ሊጠቀሱ ይችላሉ።

Downloads

Published

2024-05-06

How to Cite

Internal Conflicts within the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church and its Resolutions: The case of two Churches in Addis Ababa Diocese : Kesis Dr. Bitew Kassaw Belay. (2024). Journal-of-Ethiopian-Church-Studies/የኢትዮጵያ-ቤተ-ክርስቲያን-ጥናት-መጽሔት-Live/, 9(9), 116–151. Retrieved from https://journals.eotcmk.org/index.php/files/article/view/60