ETHINICIZATION OF RELIGIOUS CONFLICTS IN EOTC: THE CASE OF ‘WELISO TOWN’ IN OROMIA NATIONAL REGIONAL STATE

Mesfin Abate

Abstract

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ሀገር ከዋለቻቸው ታላላቅ ውለታዎች አንዱና ዋነኛው የሀገሪቱ የአንድነት ኀይል ወይም ምሰሶ ሆና ለዘመናት መቆየቷ ነው፡፡ ነገር ግን አሁን አሁን ይህ ታላቅ አስተዋፅኦ በሀይማኖት ብሔርተኝነት ሳቢያ ፈተና ላይ እየወደቀ ነው፡፡ በዚህም ሀገሪቱም ቤተ ክርስቲያኗም አደጋ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ከአማራ እና ትግራይ ብሔሮች ጋር ታሪካዊ ትስስርና ዝምድና አላት በሚል ግንዛቤ የአስተዳደር ፖለቲካዊ ጫናው በርትቶባታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ አንዳንድ ፖለቲከኞች/ቡድኖች ቤተ ክርስቲያንን አምርረው የሚተቹትና የሚቃወሙት ከዚሁ ከተቀናቃኝ ብሔሮች ጋር አላት ከሚባለው ታሪካዊ ግንኙነትና ዝምድና በመነሳት ነው፡፡ በርግጥ የሃይማኖት ብሔርተኝነት ግጭት ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ፖለቲካዊ እና/ወይም ኢኮኖሚያዊ በሆኑ ምክንያቶችና ተፅዕኖዎች አማካይነት ሊከሰት ይችላል፡፡ የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (በተለይም በወሊሶ ከተማ) የሃይማኖት ብሔርተኝነት ግጭትን ምንነት፣ ሰበብ እና ተዋናይ አካላት መለየትና መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ ገላጭ የምርምር ዘዴን የተጠቀመ ሲሆን፣ መረጃዎች ከአሥራ ሁለት ቁልፍ መረጃ ሰጪዎች ተሰብስበዋል፡፡ ለመረጃ ሰጭነት ከተመረጡት መካከል የከተማው ከፍተኛ አስተዳደር ባለሥልጣናት፣ የፖሊስ አባላት እና የኅብረተሰብ መሪዎችን ይጠቀሳሉ፡፡ የሰነድ ፍተሻ፣ ቃለ መጠይቅ እና ምልከታ የጥናቱ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ናቸው። በጥናቱ ግኝት እንደተመለከተውና በመፍትሔ ሐሳብ ክፍል እንደተጠቆመው፣ ቤተ ክርስቲያን ይህንን የተሳሳተ ትርክት ለማረምና ለማስተካከል ተገቢ የግንዛቤ ትምህርት በመስጠትና ከልዩ ልዩ የፖለቲካ መሪዎችና ቡድኖች እንዲሁም ልዩ ልዩ ጎሳ ካላቸው የእምነቱ ተከታዮች ጋር ውይይት በማድረግ ችግሮችን መፍታትና የወደፊት ሕልውናዋን ማረጋገጥ ይገባታል፡፡

Downloads

Published

2024-05-06

How to Cite

ETHINICIZATION OF RELIGIOUS CONFLICTS IN EOTC: THE CASE OF ‘WELISO TOWN’ IN OROMIA NATIONAL REGIONAL STATE: Mesfin Abate. (2024). Journal-of-Ethiopian-Church-Studies/የኢትዮጵያ-ቤተ-ክርስቲያን-ጥናት-መጽሔት-Live/, 9(9), 88–115. Retrieved from https://journals.eotcmk.org/index.php/files/article/view/59