A Holistic Approach to Human Health: Exploring the Role of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
Taddese Alemu Zerfu1 , Zenebu Begna2 and Addisalem Genta3
Abstract
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተከታዮቿን እምነትና ተግባር በመምራት ረገድ ከፍተኛ ሚና አላት። የትምህርቶቹ ዋና ዋና ተግባራት እንደ ጾም፣ ጸሎት፣ ይቅርታ እና የማኅበረሰብ ተሳትፎን የመሳሰሉ መንፈሳዊ እና አካላዊ ደኅንነትን የሚያበረታቱ መርሖዎች ናቸው። ነገር ግን በጤና ላይ በተለይም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ ያላቸው ሚና እና ልዩ ተፅዕኖ ገና በበቂ መጠን አልተመረመረም። ይህ ጥናት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ክርስቲያናዊ ልምምዶች እና በሰው ልጅ ጤና እና ደኅንነት መካከል ያለውን የተወሳሰበ ግንኙነት ለመመርመር ያለመ ነው። በዚህ ጥናት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን ትምህርት፣ ቀኖና እና ትውፊት በጥልቀት በመመርመር እንደ ጾም፣ ጸሎት፣ ይቅርታ እና የኅብረተሰብ ተሳትፎ ተግባራት አካላዊ፣ አእምሯዊ እና ማኅበራዊ ደኅንነትን በማስተዋወቅ ረገድ ያለውን ሚና በጥልቀት ። በተጨማሪም የቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ሰነዶች እና ጽሑፎች መርምረናል ። ከሃይማኖት አባቶች እና ከሕክምና ባለሙያዎች ጋር የአንድ ለአንድ ውይይት እና ምክክር አድርገናል። የጥናታችን ግኝቶች እንደሚያሳዩት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የክርስትና ሕይወት ዘይቤን መከተል ከልዩ ልዩ አዎንታዊ የጤና ውጤቶች ጋር በጥብቅ የተቆራኘ መሆኑን አሳይተዋል። በተለይም እንደ ጾም ያሉ ልምምዶች ክብደትን ከመቆጣጠር፣ ጤናን በማሻሻል (improved metabolic health) እና እንደ ስኳር በሽታ እና የልብና የደም ሥር (cardiovascular) ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ተጋላጭነትን በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንሱት እንደሚችሉ ተረድተናል። ጸሎት እና ይቅርታ ደግሞ በአእምሮ ጤና ላይ ጠቃሚ ተጽዕኖዎች እንዳሉት፤ ስሜታዊ ጥንካሬን እና ለአጠቃላይ ጤና እና ደኅንነት ወሳኝ የሆኑትን ማኅበራዊ ግንኙነቶችን እና ማኅበራዊ መረቦችን በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምሩ እንደሚችሉ ተረድተናል። በተጨማሪም በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ማኅበረሰብ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ለአጠቃላይ ጤና እና ደኅንነት ወሳኝ የሆኑ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ማሻሻል እንደሚችሉ አረጋግጠናል። ጥናቱ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የክርስትና ሕይወት ዘይቤን መከተል የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ጤናን በማሳደግ እና በሽታን በመከላከል ረገድ ያለውን ሚና አጉልቶ አሳይቷል። በተለይም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ተከታዮች የሕይወት ዘይቤ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ተጋላጭነትን በመንፈሳዊ እና በአካላዊ ልምምዶች ከማሻሻል በተጨማሪ የአእምሮ እና ማኅበራዊ ጤናን እንዲሁም አጠቃላይ የሰው ልጅ ደኅንነትን እንደሚያሳድግ ታምኖበታል። ስለዚህ የሕዝብ ጤናን ለማሻሻል የሃይማኖትና የጤና ተቋማት በጋራ እንዲሠሩ እንመክራለን። በሌላ መልኩ ግን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮ በሰው ልጅ ሁለንተናዊ ጤና ላይ የሚያመጣውን ተጽዕኖ የበለጠ ለማወቅና የተሟላ ግንዛቤ ለማግኘት፤ ከሕዝብ ጤና ፖሊሲዎች ጋር ለማዋሐድ ተጨማሪ ጥናቶች እንዲካሄዱ እንጠቁማለን ።