Economic Valuation of Tangible and Intangible Assets of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church: A Review of Possible Quantifications and ways forward
Mintewab Bezabih and Feleke Asrat
Abstract
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበርካታ ሀብታት ባለቤት፣ እንዲኹም ለብዙኃን የኩራት እና የመመኪያ ምንጭ ነች። በመኾኗም ያሏት ሀብታት በአግባቡ ሊጠበቁ፣ ይዘታቸውን በጠበቀ መልኩ እድሳት ሊደረግላቸው እና ዘላቂ ጥቅም ሊሰጡ እንዲችሉ ለማድረግ በጣም ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ የሚካድ አይደለም፡፡ ነገር ግን እነዚህን ሀብታት በአግባቡ ለመመዝገብ፣ ለማደራጀት እና የባለቤትነት መብትን ባረጋገጠ መልኩ ለመጠቀም የሚያስችል የተዋቀረ ሥርዓት ባለመኖሩ ወይም እብዛም በመኾኑ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያሏትን ሀብታት ለማስተዋወቅም ኾነ ከሀብቶቿ ልታገኝ የሚገባትን ጥቅም እንዳታገኝ ትልቅ ፈተና ኾኗል፡፡ ይኽንኑ መሠረት በማድረግ ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ሀብታትን የመለየት እና በምጣኔ ሀብት (ኢኮኖሚክስ) ንድፈ ሐሳብ ውስጥ የተካተቱትን በጣም ተገቢ የኾኑ የንብረት ግምገማ ቴክኒኮችን በመገምገም ቀደምት የጥናት እና ምርምር ውጤቶች (ተዛማጅ ጽሑፎችን) ክለሳ ባደረገ ዘዴ ላይ ተመርኩዞ ቀርቧል፡፡ ጥናቱ ሦስት ውጤቶችን አካቷል፡፡ በመጀመሪያ ጥናቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሀብታትን በዐምስት ከፍሏል (ለንብረት ግምገማ ምቹ በኾኑት ላይ በማተኮር) እነዚህም አካላዊ ንብረቶች፣ አእምሯዊ ሀብቶች፣ ባህላዊ እሴቶች (የሚዳሰስ እና የማይዳሰሱ)፣ ከአካላዊ እና አእምሯዊ ደኅንነት ጋር የተያያዙ ንብረቶች፣ እንዲሁም የተፈጥሮ እና ሥነ ምኅዳራዊ (ኢኮሎጂካል) ንብረቶች ሲኾኑ፤ በኹለተኛ ደረጃ ጥናቱ ተጓዳኝ ንብረቶችን ዋጋ ለመስጠት በጣም ተገቢ የኾኑትን የግምገማ ዘዴዎችን ለይቷል፡፡ በመጨረሻም፣ በቀጣይ በቤተ ክርቲያኒቱ የንብረት ምዘና ጥናት ለማካሄድ መሰናክል ኾነው ሊቀርቡ የሚችሉ ኹኔታዎችን በቅድመ ማስጠንቀቂያነት በመለየት አቅርቧል፡፡